እስራኤልም በሰይፍ መታው፤ ምድሩንም ከአርኖን ጀምሮ እስከ አሞን ልጆች እስከ ያቦቅ ድረስ ወረሰ፤ የአሞንም ልጆች ዳርቻ ኢያዜር ነበረ።
ኢያሱ 8:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ተከትለዋቸው በነበረበት በተራራው ቍልቍለትና በምድረ በዳ የጋይን ሰዎች መግደልን ከጨረሱ፥ ሁሉንም በጦር ወግተው ከአጠፉአቸው በኋላ ኢያሱ ወዲያውኑ ወደ ጋይ ተመልሶ፥ በሰይፍ አጠፋት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን የጋይን ወንዶች ሁሉ ባሳደዷቸው ሜዳና ምድረ በዳ ከጨረሷቸውና እያንዳንዳቸውንም በሰይፍ ከፈጁ በኋላ፣ ወደ ከተማዪቱ ተመልሰው በዚያ ያገኙትን ሁሉ ገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ፤ እስራኤልን ሊያሳድዱ ሄደው የነበሩትን የጋይን ሰዎች ሁሉ በሜዳና በምድረ በዳ ከገደሉአቸው በኋላ፥ እነርሱም በሰይፍ ስለት እስኪያልቁ ድረስ ከፈጁአቸው በኋላ፥ እስራኤል ሁሉ ወደ ጋይ ተመለሱ፥ በሰይፍም ስለት መቱአት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን በሜዳና በምድረ በዳ ቀደም ሲል የዐይ ወታደሮች እነርሱን አሳደዋቸው በነበረው ስፍራ ሁሉንም ገድለው ከጨረሱ በኋላ ወደ ዐይ ከተማ ገብተው በዚያ የተረፉትንም በሰይፍ ፈጁአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ እስራኤልን ሊያሳድዱ ሄደው የነበሩትን የጋይን ሰዎች ሁሉ በሜዳና በምድረ በዳ ከገደሉአቸው በኋላ፥ እነርሱም በሰይፍ ስለት እስኪያልቁ ድረስ ከወደቁ በኋላ፥ እስራኤል ሁሉ ወደ ጋይ ተመለሱ፥ በሰይፍም ስለት መቱአት። |
እስራኤልም በሰይፍ መታው፤ ምድሩንም ከአርኖን ጀምሮ እስከ አሞን ልጆች እስከ ያቦቅ ድረስ ወረሰ፤ የአሞንም ልጆች ዳርቻ ኢያዜር ነበረ።
ከእስራኤልም ሰዎች ፊት ወደ ምድረ በዳ መንገድ ሸሹ፤ ሰልፉም ደረሰባቸው፤ ከየከተማውም የወጡት በመካከላቸው ገደሉአቸው።