የያዕቆብም ልጆች ከምድረ በዳ መጡ፤ ይህንም በሰሙ ጊዜ ፈጽመው ደነገጡ፤ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፤ እጅግም ተቈጡ፤ እንዲህ አይደረግምና።
ኢያሱ 7:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምልክት የታየበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል አድርጎአልና፥ እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕርሙ የተገኘበት ሰው፣ እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት ይቃጠላል፤ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሷል፤ በእስራኤልም ዘንድ አሳፋሪ ተግባር ፈጽሟልና።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርም የሆነውም ነገር የተገኘበት ሰው የጌታን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል ፈጽሟልና እርሱና የእርሱ የሆነው ነገር ሁሉ በእሳት ይቃጠል።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርም የሆኑ (የተከለከሉ) ነገሮች የተገኙበትም ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ስላፈረሰና በእስራኤል ላይ በደል ስለ ፈጸመ እርሱና የእርሱ የሆነ ሁሉ በእሳት ይቃጠል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርም የሆነውም ነገር የተገኘበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል አድርጎአልና እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ። |
የያዕቆብም ልጆች ከምድረ በዳ መጡ፤ ይህንም በሰሙ ጊዜ ፈጽመው ደነገጡ፤ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፤ እጅግም ተቈጡ፤ እንዲህ አይደረግምና።
እኔም ነውሬን ወዴት እጥላታለሁ? አንተም በእስራኤል ዘንድ ከሰነፎች እንደ አንዱ ትሆናለህ፤ እንግዲያስ ለንጉሡ ንገረው፥ እኔንም አይነሣህም” አለችው።
ሕዝቡ በድለዋል፤ ከእነርሱም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል፤ እርም ከሆነውም ነገር ሰርቀው ወሰዱ፤ በዕቃቸውም ውስጥ ሸሸጉት።
በእስራኤል ላይ ስላደረጉት ስንፍና ሁሉ የብንያም ገባዖንን ይወጉ ዘንድ ለሚሄዱ ሕዝብ በመንገድ ስንቅ የሚይዙ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ከመቶው ዐሥር ሰው፥ ከሺሁም መቶ ሰው፥ ከዐሥሩም ሺህ አንድ ሺህ ሰው እንወስዳለን።”
የገባዖንም ሰዎች ተነሡብን፤ ቤቱንም በሌሊት በእኛ ላይ ከበቡት፤ ሊገድሉኝም ወደዱ፤ ዕቅብቴንም አዋረድዋት፤ አመነዘሩባትም፤ እርስዋም ሞተች።
እኔም ዕቅብቴን ይዤ በመለያያዋ ቈራረጥኋት፤ በእስራኤልም ዘንድ እንደዚህ ያለ ስንፍና ስለ ሠሩ ወደ እስራኤል ርስት አውራጃ ሁሉ ሰደድሁ።
ሳኦልም፥ “በድያለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በዐይንህ ፊት ከብራለችና ከዚህ በኋላ ክፉ አላደርግብህም፤ እነሆ፥ ስንፍና እንደ አደረግሁና፥ እጅግ ብዙም እንደ ሳትሁ ዐወቅሁ” አለ።