ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፥ “አምላካችን እግዚአብሔርን አመስግኑ” አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፥ በጕልበታቸውም ተንበርክከው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ ደግሞም ለንጉሡ።
ኢያሱ 22:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገሩም የእስራኤልን ልጆች ደስ አሰኘ፤ ለእስራኤልም ልጆች በነገሩአቸው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከዚያም ወዲያ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ የተቀመጡባትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ለመውጋት አንወጣም ተባባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያንም ይህን ሲሰሙ ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከዚያም የሮቤልና የጋድ ወገኖች የሚኖሩበትን አገር በጦርነት ለማጥፋት የመሄድን ነገር አላነሡም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገሩም የእስራኤልን ልጆች ደስ አሰኘ፤ የእስራኤልም ልጆች ጌታን አመሰገኑ፥ ከዚያም ወዲያ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የተቀመጡባትን ምድር ለማጥፋት ወጥተን እንወጋታለን ብለው አልተናገሩም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያንም በመልሱ ረክተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከዚያም በኋላ የሮቤልና የጋድ ሕዝብ የሚኖሩባትን ምድር ለመደምሰስ ጦርነት ስለ ማንሣት ጉዳይ መናገር አልፈለጉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገሩም የእስራኤልን ልጆች ደስ አሰኘ፥ የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን አመሰገኑ፥ ከዚያም ወዲያ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የተቀመጡባትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ወጥተው እንዲወጉአቸው አልተናገሩም። |
ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፥ “አምላካችን እግዚአብሔርን አመስግኑ” አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፥ በጕልበታቸውም ተንበርክከው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ ደግሞም ለንጉሡ።
ያንጊዜም ሕዝቡ ሁሉ ጸጥ ብለው እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያደረገላቸውን ተአምራትና ድንቅ ሥራ ሁሉ ሲናገሩ ጳውሎስንና በርናባስን አዳመጡአቸው።
በመምጣቱ ብቻ አይደለም፤ በአጽናናችሁት ማጽናናትም ነው እንጂ፤ ለእኛ እንደምታስቡና እንደምትቀኑ ፍቅራችሁን ነግሮናል፤ ይህንም ሰምቼ ደስታዬ በእናንተ በዛ።
በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን።
ካህኑ ፊንሐስና የማኅበሩ አለቆች፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት የእስራኤል መሳፍንት ሁሉ ፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ የተናገሩትን ቃል በሰሙ ጊዜ ዝም አሉ፤ ደስም አሰኛቸው።
የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ከእርሱም ጋር የማኅበሩ አለቆች ከሮቤል ልጆችና ከጋድ ልጆች፥ ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ዘንድ ከገለዓድ ሀገር ወደ ከነዓን ሀገር ወደ እስራኤል ልጆች ተመለሱ፤ ወሬም አመጡላቸው።