ኢያሱ 22:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ለእስራኤል አእላፋት አለቆች እንዲህ ብለው መለሱላቸው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የሮቤልና የጋድ ነገዶች እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ ለእስራኤል ጐሣ መሪዎች እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ ለእስራኤል ነገድ አለቆች እንዲህ ብለው መለሱላቸው፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሮቤል፥ የጋድና በምሥራቅ የሚኖሩት የምናሴ ነገዶች ሕዝብም ለምዕራብ ነገዶች የቤተሰብ መሪዎች እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ ለእስራኤል አእላፋት አለቆች እንዲህ ብለው መለሱላቸው፦ |
አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።
የዛራ ልጅ አካን እርም ነገር በመውሰድ ኀጢአትን ስለ ሠራ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ቍጣ አልወረደምን? እርሱም ብቻውን ቢበድል በኀጢአቱ ብቻውን ሞተን?”
“እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ጌታም ነው፤ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ ነው፤ እርሱ ያውቃል። እስራኤልም ያውቀዋል። በእግዚአብሔር ፊት ያደረግነው ለበደልና ለመካድ ከሆነ ዛሬ አያድነን፤
ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።