ሙሴም ከእስራኤል ሁሉ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መረጠ፤ በሕዝቡም ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የአምሳም አለቆች፥ የዐሥርም አለቆች አድርጎ ሾማቸው።
ኢያሱ 22:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐሥር አለቆችም ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ አንድ አንድ የእየአባቶቻቸው ቤት አለቃ፤ እያንዳንዱም በእስራኤል አእላፋት መካከል የአባቶቻቸው ቤት አለቃ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱም ጋራ እያንዳንዱን የእስራኤልን ነገድ የሚወክሉ ዐሥር አለቆች ዐብረው ላኩ፤ እነዚህም እያንዳንዳቸው ከእስራኤላውያን ጐሣዎች የተውጣጡ የየቤተ ሰቡ አለቆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም ጋር ዐሥር አለቆች ነበሩ፥ ከእስራኤል ከየነገዱ ሁሉ አንድ አንድ የአባቶች ቤት አለቃ፤እንያንዳንዱም በእስራኤል አእላፋት መካከል የእየአባቶቻቸው ቤት አለቆች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፊንሐስም ጋር ዐሥር ታላላቅ ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህም እያንዳንዱ በምዕራብ ከሚገኙት ነገዶች የተውጣጡ በየጐሣቸው የቤተሰብ መሪዎች ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም ጋር አሥር አለቆች ነበሩ፥ ከእስራኤል ከየነገዱ ሁሉ አንድ አንድ የአባቶች ቤት አለቃ፥ እንያንዳንዱም በእስራኤል አእላፋት መካከል የእየአባቶቻቸው ቤት አለቃ ነበረ። |
ሙሴም ከእስራኤል ሁሉ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መረጠ፤ በሕዝቡም ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የአምሳም አለቆች፥ የዐሥርም አለቆች አድርጎ ሾማቸው።
በገለዓድም ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች፥ ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ ደረሱ፤ እንዲህም ብለው ነገሩአቸው