ኢያሱ 22:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች በከነዓን ምድር ዳርቻ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በገለዓድ፥ የእስራኤል ልጆች ባሉበት ወገን፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ መሠዊያ እንደ ሠሩ ሰሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤላውያን ይዞታ በሆነችው በከነዓናውያን ምድር ወሰን በገሊሎት ላይ የሮቤልና የጋድ፣ እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ መሠዊያ መሥራታቸውን ሌሎቹ እስራኤላውያን በሰሙ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች እንዲህ የሚል ወሬ ሰሙ፦ “እነሆ፥ በከነዓን ምድር ዳርቻ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው ግዛት፥ የእስራኤል ልጆች ባሉበት ወገን፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ መሠዊያ ሠርተዋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀሩትም የእስራኤል ሕዝብ የሮቤል፥ የጋድና በምሥራቅ ያሉት የምናሴ ነገዶች በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ በከነዓን ምድር በምትገኘው በእስራኤላውያን ይዞታ በሆነችው በገሊሎት መሠዊያ መሥራታቸውን ሰሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤልም ልጆች፦ እነሆ፥ በከነዓን ምድር ዳርቻ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው ግዛት፥ የእስራኤል ልጆች ባሉበት ወገን፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ መሠዊያ ሠርተዋል የሚል ወሬ ደረሰላቸው። |
ከሳምንቱም በመጀመሪያዉ ቀን ማርያም መግደላዊት በማለዳ ገና ጨለማ ሳለ ወደ መቃብር መጣች፤ ድንጋዩንም ከመቃብሩ አፍ ተነሥቶ አገኘችው።
ሁለት መላእክትንም ነጭ ልብስ ለብሰው የጌታችን የኢየሱስ ሥጋ በነበረበት ቦታ አንዱ በራስጌ፥ አንዱም በግርጌ ተቀምጠው አየች።
በዚያን ጊዜ አምላካችሁ እግዚአብሔር ስሙ ይጠራበት ዘንድ ወደዚያ ወደ መረጠው ስፍራ፥ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ቍርባናችሁንም፥ ዐሥራታችሁንም፥ ከእጃችሁ ሥራ ቀዳምያቱን የተመረጠውንም መባችሁን ሁሉ፥ ለአምላካችሁም የተሳላችሁትን ሁሉ ውሰዱ።
በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ ዮርዳኖስ አቅራቢያም ወደ ገለዓድ በመጡ ጊዜ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዚያ በዮርዳኖስ አጠገብ የሚታይ ታላቅ መሠዊያ ሠሩ።
የእግዚአብሔር ማኅበር ሁሉ የሚለው ይህ ነው፥ “ዛሬ እግዚአብሔርን መከተልን ትተዉ ዘንድ፥ መሠዊያም ትሠሩ ዘንድ፥ እግዚአብሔርንም ዛሬ ትክዱት ዘንድ ይህ በእስራኤል አምላክ ፊት ያደረጋችሁት ኀጢአት ምንድን ነው?
ነገር ግን የርስታችሁ ምድር ቢያንሳችሁ የእግዚአብሔር ማደሪያ ወደሚቀመጥበት ወደ እግዚአብሔር ርስት ምድር አልፋችሁ ከእኛ ጋር ውረሱ፤ ከአምላካችንም ከእግዚአብሔር መሠዊያ ውጭ ለእናንተ መሠዊያ ሠርታችኋልና እግዚአብሔርን አትካዱ፤ እግዚአብሔርንም አትተዉት።
የገለዓድ ሰዎችም ኤፍሬም በሚያልፍበት በዮርዳኖስ ማዶ ደረሱባቸው። ከዚህ በኋላ ከኤፍሬም ያመለጡት እንሻገር ባሉ ጊዜ የገለዓድ ሰዎች፥ “በውኑ እናንተ ከኤፍሬም ወገን ናችሁን?” ቢሉአቸው “አይደለንም” አሉ።