የአቤሴሎምም አገልጋዮች ወደ ሴቲቱ ወደ ቤት መጥተው፥ “አኪማሆስና ዮናታን የት አሉ?” አሉ፤ ሴቲቱም፥ “ፈፋውን ተሻግረው ሄዱ፤ ጥቂትም ቀደሙአችሁ” አለቻቸው። እነርሱም ፈልገው አጡአቸው፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሱ።
ኢያሱ 2:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ወጥተው ወደ ተራራው ሄዱ፤ የሚከተሉአቸውና የሚፈልጉአቸውም እስኪመለሱ ሦስት ቀን በዚያ ተቀመጡ፤ በመንገዱም አላገኙአቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ወጥተው ወደ ኰረብቶቹ ሄዱ፤ የሚከታተሏቸውም ሰዎች በየመንገዱ ሁሉ ላይ ፈልገውና ዐጥተው እስኪመለሱ ድረስ፣ ሦስት ቀን በዚያው ተሸሸጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ሄደው ወደ ተራራው ደረሱ፥ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ ሦስት ቀን በዚያ ተቀመጡ፤ አሳዳጆቹም በመንገዱ ሁሉ ፈልገው አላገኙአቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሳዳጆቻቸው በየመንገዱ ሁሉ ፈልገው ከአጡአቸው በኋላ እስከ ተመለሱ ድረስ ሰዎቹ ወደ ተራራማው አገር ሄደው ለሦስት ቀኖች ተደበቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ሄደው ወደ ተራራው ደረሱ፥ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ ሦስት ቀን በዚያ ተቀመጡ፥ አሳዳጆቹም በመንገዱ ሁሉ ፈልገው አላገኙአቸውም። |
የአቤሴሎምም አገልጋዮች ወደ ሴቲቱ ወደ ቤት መጥተው፥ “አኪማሆስና ዮናታን የት አሉ?” አሉ፤ ሴቲቱም፥ “ፈፋውን ተሻግረው ሄዱ፤ ጥቂትም ቀደሙአችሁ” አለቻቸው። እነርሱም ፈልገው አጡአቸው፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሱ።
እርስዋም፥ “እንደ ቃላችሁ ይሁን” አለች፤ አሰናበተቻቸውም፤ እነርሱም ሄዱ፤ ቀዩንም ፈትል በመስኮቱ በኩል አንጠለጠለችው።
ሁለቱም ጐልማሶች ተመለሱ፤ ከተራራውም ወርደው ተሻገሩ፤ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ መጡ፤ የደረሰባቸውንም ሁሉ አወሩለት።