La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የአ​ባ​ቴን ቤት፥ እና​ቴ​ንም፥ ወን​ድ​ሞ​ቼ​ንና ቤቴ​ንም ሁሉ፥ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አድኑ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንም ከሞት አድኑ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የአባቴንና የእናቴን፣ የወንድሞቼንና የእኅቶቼን እንዲሁም የእነርሱ የሆነውን ነፍስ ሁሉ እንድታተርፉልኝ፤ ከሞትም አድኑን።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አባቴንና እናቴንም ወንድሞቼንና እኅቶቼንም ያላቸውንም ሁሉ አድኑ፥ ነፍሳችንንም ከሞት ታደጉ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አባቴንና እናቴን፥ ወንድሞቼን፥ እኅቶቼንና የእነርሱን ቤተሰቦች ሁሉ ከሞት ለማዳን ቃል ግቡልኝ!”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አባቴንና እናቴንም ወንድሞቼንና እኅቶቼንም ያላቸውንም ሁሉ እንድታድኑ፥ ሰውነታችንንም ከሞት እንድታድኑ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 2:13
3 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማሉ​ልኝ፤ እኔ ለእ​ና​ንተ ቸር​ነት እንደ አደ​ረ​ግሁ እና​ንተ ደግሞ ለአ​ባቴ ቤት ቸር​ነት እን​ድ​ታ​ደ​ርጉ፥ በእ​ው​ነት ምል​ክት ስጡኝ።


ሰዎ​ቹም፥ “ሕይ​ወ​ታ​ች​ንን ስለ እና​ንተ አሳ​ል​ፈን ለሞት እን​ሰ​ጣ​ለን” አሉ፤ እር​ስ​ዋም አለች፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን በሰ​ጣ​ችሁ ጊዜ ቸር​ነ​ት​ንና ጽድ​ቅን ታደ​ር​ጉ​ል​ና​ላ​ችሁ።” ሰዎ​ቹም፥ “ይህን ነገ​ራ​ች​ንን ባት​ገ​ልጪ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሀገ​ራ​ች​ሁን በእ​ው​ነት አሳ​ልፎ ከሰ​ጠን ከአ​ንቺ ጋር ቸር​ነ​ትን እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሏት።


እነ​ዚ​ያም ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሰ​ለሉ ሁለቱ ጐል​ማ​ሶች ወደ ዘማ​ዪቱ ረዓብ ቤት ገብ​ተው ረዓ​ብን፥ አባ​ቷ​ንና እና​ቷን፥ ወን​ድ​ሞ​ች​ዋ​ንም፥ ያላ​ት​ንም ሁሉ፥ ቤተ ዘመ​ዶ​ች​ዋ​ንም ሁሉ አወ​ጡ​አ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰፈር በውጭ አስ​ቀ​መ​ጡ​አ​ቸው።