ኢያሱ 19:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስከ ባሌቅ ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ያሉ መንደሮቻቸው ሁሉ ናቸው። ይህም በባሜት ላይ ወደ ደቡብ ያልፋል። የስምዖን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም እስከ ባዕላትብኤር ወይም ኔጌብ ውስጥ እስካለው እስከ ራሞት ድረስ ባሉት ከተሞች ዙሪያ የሚገኙት መንደሮች ሁሉ ከእነዚሁ ጋራ ይጠቃለላሉ። እንግዲህ በየጐሣው የተደለደለው የስምዖን ነገድ ርስት ይህ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስከ ባዕላት-ብኤርና እስከ ደቡቡ ራማት ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ያሉ መንደሮች ሁሉ። የስምዖን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደቡብ በኩል እስከምትገኘው እስከ ባዕላትበኤር (ራማ) ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ያሉትን ትንንሽ ከተሞችን ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ የስምዖን ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይዞ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስከ ባዕላትብኤርና እስከ ደቡቡ ራማት ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ያሉ መንደሮች ሁሉ። የስምዖን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። |
ከይሁዳ ልጆች ክፍል የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ፤ የይሁዳም ልጆች ዕድል ፋንታ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸው መካከል ወረሱ።