ዳዊትም፥ “በበሩ አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ማን ባጠጣኝ?” ብሎ ተመኘ። ያንጊዜም የፍልስጥኤማውያን ኀይል በቤተ ልሔም ነበረ።
ኢያሱ 19:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃጠናት፥ ናባሐል፥ ሲምዖን፥ ኢያሪሆ፥ ቤቴሜንም፤ ዐሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ቀጣትን፣ ነህላልን፣ ሺምሮንን፣ ይዳላንና ቤተ ልሔምን ይጨምራል፤ እነዚህም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ ሁለት ከተሞች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀጣት፥ ነህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላ፥ ቤተልሔም፤ ዐሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ቃጣት፥ ናህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላና ቤተልሔም ተብለው የሚጠሩትን ዐሥራ ሁለት ከተሞችና በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ያጠቃልላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀጣት፥ ነህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላ፥ ቤተ ልሔም፥ አሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
ዳዊትም፥ “በበሩ አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ማን ባጠጣኝ?” ብሎ ተመኘ። ያንጊዜም የፍልስጥኤማውያን ኀይል በቤተ ልሔም ነበረ።
ዛብሎንም በቄድሮንና በአማን የሚኖሩትን ሰዎች አላጠፋቸውም፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በመካከላቸው ተቀመጡ፤ ግብርም የሚገብሩላቸው ሆኑ።
ሁለቱም እስከ ቤተ ልሔም ድረስ ሄዱ። ወደ ቤተ ልሔምም በደረሱ ጊዜ የከተማይቱ ሰዎች ሁሉ ስለ እነርሱ፦ ይህች ኑኃሚን ናትን? እያሉ ተንጫጩ።