ገባዖን ፈጽማ ትሰፋ ነበርና በዚያ መሥዋዕት ይሠዋ ዘንድ ተነሥቶ ሄደ፤ ሰሎሞንም በዚያ መሠዊያ ላይ በገባዖን አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዋ።
ኢያሱ 18:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብንያምም ልጆች ነገድ ከተሞች በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ ኢያሪኮ፥ ቤትሖግሊ፥ ዐመቀስስ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የብንያም ነገድ በየጐሣቸው የያዟቸው ከተሞች እነዚህ ናቸው፤ ኢያሪኮ፣ ቤትሖግላ፣ ዓመቀጺጽ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የብንያምም ልጆች ነገድ ከተሞች በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ ኢያሪኮ፥ ቤትሖግላ፥ ዓመቀጺጽ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የብንያም ነገድ ከተሞች በየወገናቸው ቤትሖግላ፥ ዔሜቀጺጽ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብንያምም ልጆች ነገድ ከተሞች በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፥ ኢያሪኮ፥ ቤትሖግላ፥ ዓመቀጺጽ፥ |
ገባዖን ፈጽማ ትሰፋ ነበርና በዚያ መሥዋዕት ይሠዋ ዘንድ ተነሥቶ ሄደ፤ ሰሎሞንም በዚያ መሠዊያ ላይ በገባዖን አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዋ።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ይወርድ ነበር፤ ሽፍቶችም አገኙት፤ ደበደቡት፥ አቈሰሉት፥ ልብሱንም ገፍፈው፤ በሕይወትና በሞት መካከል ጥለውት ሄዱ።
ከዚያም ድንበራቸው ወደ ቤተ ገለዓም ይወጣል፤ በቤትዓረባ በሰሜን በኩል ያልፋል፤ ድንበራቸውም ወደ ሮቤል ልጅ ወደ ሊቶን ቢዮን ይወጣል፤
በሰሜን በኩል ድንበራቸው ከዮርዳኖስ ጀመረ፤ ድንበሩም ከኢያሪኮ አዜብ ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፥ ከዚያም በተራራማው ሀገር ወደ ባሕር ወጣ፤ መውጫውም የቤቶን ምድብራይጣስ ነበረ።
የድንበራቸውም ፍጻሜ በሰሜን በኩል ወደ ጨው ባሕር ልሳን ይደርሳል፤ በደቡብም በኩል ድንበራቸው ዮርዳኖስ ነው። ይህም በደቡብ በኩል ያለው ድንበር ነው።
የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ “ውጡና ምድሪቱን ኢያሪኮን እዩ” ብሎ ከሰጢም ሁለት ጐልማሶች ሰላዮችን በስውር ላከ። እነዚያም ሁለት ጐልማሶች ሄዱ፤ ወደ ኢያሪኮም ደረሱ፤ ረዓብ ወደሚሉአትም ዘማ ቤት ገቡ፤ በዚያም ዐደሩ።
የቄናዊው የሙሴ አማት የዮባብ ልጆችም ከዘንባባ ከተማ ተነሥተው ከዓራድ በአዜብ በኩል ወዳለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወደ ይሁዳ ልጆች ሄደው ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ።