La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 13:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ድን​በ​ራ​ቸ​ውም በአ​ር​ኖን ሸለቆ ዳር ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ በሸ​ለ​ቆው መካ​ከል ያለ​ችው ከተማ፥ ሜሶ​ርም ሁሉ፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ድንበራቸው ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ካለው ከአሮዔርና ከሸለቆው መካከል ካለችው ከተማ አንሥቶ ያለው ግዛት ሲሆን፣ ሜድባ አጠገብ ያለውን ደጋውን አገር በሙሉ፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ግዛታቸውም በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ በሸለቆው መካከል ያለችው ከተማ፥ የሜድባ ሜዳ ሁሉ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ግዛታቸውም በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ እስከሚገኘው እስከ ዓሮዔርና በዚያም ሸለቆ መካከል እስካለችው ከተማ አልፎ በሜደባ ዙሪያ ያለውን ሜዳማ አገር ሁሉ ያጠቃልላል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ድንበራቸውም በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ በሸለቆው መካከል ያለችው ከተማ፥ የሜድባ ሜዳ ሁሉ፥

Ver Capítulo



ኢያሱ 13:16
18 Referencias Cruzadas  

ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ገሩ፤ በጋድ ሸለቆ መካ​ከል ባለ​ች​ውም በኢ​ያ​ዜር ከተማ ቀኝ በኩል በአ​ሮ​ዔር ላይ ሰፈሩ።


ሠላሳ ሁለ​ትም ሺህ ሰረ​ገ​ሎ​ችን የሞ​ዓ​ካን ንጉ​ሥና ሕዝ​ቡ​ንም ቀጠሩ፤ መጥ​ተ​ውም በሜ​ድባ ፊት ለፊት ሰፈሩ። የአ​ሞ​ንም ልጆች ከየ​ከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ ሰልፍ መጡ።


ሐሴ​ቦ​ንና ኤል​ያሊ ጮኹ፤ ድም​ፃ​ቸ​ውም እስከ ያሳ ድረስ ይሰ​ማል፤ ስለ​ዚህ የሞ​ዓብ ወገብ ይታ​መ​ማል።


ሐሴ​ቦ​ንም የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ንጉሥ የሴ​ዎን ከተማ ነበረ፤ እር​ሱም የፊ​ተ​ኛ​ውን የሞ​ዓ​ብን ንጉሥ ወግቶ ከአ​ሮ​ኤር እስከ አር​ኖን ድረስ ምድ​ሩን ሁሉ ወስዶ ነበር።


“ይህ​ች​ንም ምድር በዚ​ያን ዘመን ወረ​ስን፤ በአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ የገ​ለ​ዓ​ድን ተራ​ራማ ሀገር እኩ​ሌታ፥ ከተ​ሞ​ቹ​ንም ለሮ​ቤ​ልና ለጋድ ነገድ ሰጠ​ኋ​ቸው።


በሐ​ሴ​ቦን የተ​ቀ​መ​ጠው፥ በአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር፥ ከሸ​ለ​ቆ​ውም መካ​ከል ጀምሮ የገ​ለ​ዓ​ድን እኩ​ሌታ እስከ ኢያ​ቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፤


ሙሴም ለሮ​ቤል ነገድ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ርስ​ትን ሰጣ​ቸው።


ሐሴ​ቦን፥ በሜ​ሶ​ርም ያሉት ከተ​ሞች ሁሉ፥ ዲቦን፥ ባሞ​ት​በ​ዐል፥ ቤት​በ​አ​ል​ም​ዖን፥


በአ​ር​ኖን ሸለቆ ዳር ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር፥ በሸ​ለ​ቆ​ውም መካ​ከል ካለ​ችው ከተማ ጀምሮ የሚ​ሶር ሜዳ ሁሉ እስከ ዲቦን ድረስ፥


ለሁ​ለቱ ነገ​ድና ለእ​ኩ​ሌ​ታው ነገድ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበር፤ ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ርስት አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።


ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክህ​ነት ርስ​ታ​ቸው ነውና ለሌዊ ልጆች በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እድል ፋንታ የላ​ቸ​ውም፤ ጋድም፥ ሮቤ​ልም፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በም​ሥ​ራቅ በኩል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ርስ​ታ​ቸ​ውን ተቀ​ብ​ለ​ዋል።”


እስ​ራ​ኤ​ልም በሐ​ሴ​ቦ​ንና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በአ​ሮ​ዔ​ርና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በአ​ር​ኖ​ንም አቅ​ራ​ቢያ ባሉት ከተ​ሞች ሁሉ ሦስት መቶ ዓመት ተቀ​ምጦ በነ​በረ ጊዜ፥ በዚያ ዘመን ስለ ምን አላ​ዳ​ን​ሃ​ቸ​ውም ነበር?


በቄ​ኔት ለነ​በሩ፥ በሳ​ፌቅ ለነ​በሩ፥ በቴ​ማት ለነ​በሩ፥