ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒቤዜቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ኤላም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ፊዶን፥ ወደ ለኪስ ንጉሥም ወደ ኤፍታ፥ ወደ አዶላም ንጉሥም ወደ ዳቤር ልኮ፥
ኢያሱ 10:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከላኪስ ወደ አዶላም አለፉ፤ ከበቡአትም፤ ወጉአትም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢያሱና ከርሱ ጋራ የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከለኪሶ ወደ ዔግሎን ዐለፉ፤ ወጓትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከለኪሶ ወደ ዔግሎም አለፉ፥ ከበቡአትም፥ ወጉአትም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ኢያሱና ሠራዊቱ ከላኪሽ ወደ ዔግሎን ዘምተው ከበባ በማድረግ አደጋ ጣሉበት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከለኪሶ ወደ ኦዶላም አለፉ፥ ከበቡአትም፥ ወጉአትም፥ |
ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒቤዜቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ኤላም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ፊዶን፥ ወደ ለኪስ ንጉሥም ወደ ኤፍታ፥ ወደ አዶላም ንጉሥም ወደ ዳቤር ልኮ፥
በዚያ ጊዜም የጋዜር ንጉሥ ኤላም ላኪስን ለመርዳት ወጣ፤ ኢያሱም አንድ ስንኳ ሳይቀር በሰይፍ ስለት እርሱንና ሕዝቡን መታ፤ የዳነም፥ ያመለጠም የለም።
እግዚአብሔርም በእስርኤል እጅ አሳልፎ ሰጣት፤ በዚያም ቀን ያዙአት፤ በሰይፍም ስለት መቱአት፤ በላኪስም እንዳደረገው ሁሉ፥ በእርስዋ ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።