ዮሐንስ 9:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ሰደቡት፤ እንዲህም አሉት፥ “አንተ የእርሱ ደቀ መዝሙር ሁን፤ እኛስ የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ በርሱ ላይ የስድብ ናዳ በማውረድ እንዲህ አሉት፤ “የዚህ ሰው ደቀ መዝሙር አንተ ነህ፤ እኛስ የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተሳድበውም “አንተ የእርሱ ደቀመዝሙር ነህ፤ እኛ ግን የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እንዲህ እያሉ ሰደቡት፦ “የእርሱስ ደቀ መዝሙር አንተ ነህ፤ እኛ ግን የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተሳድበውም፦ “አንተ የእርሱ ደቀ መዝሙር ነህ፥ እኛ ግን የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን፤ |
ሙሴ ኦሪትን ሰጥቶአችሁ የለምን? ከእናንተ አንዱ ስንኳ ኦሪትን የሚያደርግ የለም፤ እንግዲህ ልትገድሉኝ ለምን ትሻላችሁ?”
በእጃችን ሥራ እያገለገልን እንደክማለን፤ ይረግሙናል፤ እኛ ግን እንመርቃቸዋለን፤ ያሳድዱናል፤ እኛ ግን እንጸልይላቸዋለን፤ እንታገሣቸዋለንም።
ሌቦች፥ ወይም ቀማኞች፥ ወይም ሰካሮች፥ ወይም ተሳዳቢዎች፥ ወይም ነጣቂዎች፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱአትም።