ዮሐንስ 9:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳግመኛም፥ “ምን አደረገልህ? ዐይኖችህንስ እንደምን አበራልህ?” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “ምን አደረገልህ? እንዴትስ ዐይንህን ከፈተ?” ብለው ጠየቁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግመውም “ምን አደረገልህ? እንዴትስ ዐይኖችህን ከፈተ?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “ምን አደረገልህ? ዐይኖችህንስ ያዳነው እንዴት ነው?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግመውም፦ “ምን አደረገህ? እንዴትስ ዓይኖችህን ከፈተ?” አሉት። |
ፈሪሳውያንም እንዴት እንዳየ ዳግመኛ ጠየቁት፤ እርሱም፥ “በምራቁ ጭቃ አድርጎ በዐይኖች አኖረው፥ ታጥቤም አየሁ” አላቸው።
ያም ሰው መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እርሱ ኀጢኣተኛ እንደ ሆነ እኔ አላውቅም፤ እኔ ዕዉር እንደ ነበርሁ፤ አሁን ግን እንደማይ ይህን አንድ ነገር ብቻ አውቃለሁ።”
እርሱም መልሶ፥ “አትሰሙኝም እንጂ ነገርኋችሁ፤ እንግዲህ ደግሞ ምን ልትሰሙ ትሻላችሁ? እናንተም ደቀ መዛሙርቱ ልትሆኑ ትሻላችሁን?” አላቸው።