ዮሐንስ 9:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈሪሳውያንም እንዴት እንዳየ ዳግመኛ ጠየቁት፤ እርሱም፥ “በምራቁ ጭቃ አድርጎ በዐይኖች አኖረው፥ ታጥቤም አየሁ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ፈሪሳውያንም እንዴት ማየት እንደ ቻለ ጠየቁት። ሰውየውም፣ “እርሱ ዐይኔን ጭቃ ቀባኝ፤ እኔም ታጠብሁ፤ ይኸው አያለሁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ፈሪሳውያን እንዴት እንዳየ እንደገና ጠየቁት። እርሱም “ጭቃ በዐይኖቼ አኖረ፤ ታጠብሁም፤ አያለሁም፤” አላቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈሪሳውያን “እንዴት ማየት ቻልክ?” ብለው ሰውየውን እንደገና ጠየቁት። እርሱም “ዐይኖቼ ላይ ጭቃ አደረገልኝና ታጠብኩ፤ ከዚያም በኋላ ማየት ቻልኩ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ፈሪሳውያን ደግሞ እንዴት እንዳየ እንደ ገና ጠየቁት። እርሱም፦ “ጭቃ በዓይኖቼ አኖረ ታጠብሁም አያለሁም” አላቸውም። |
ዳግመኛም ዕዉሩን፥ “አንተ ስለ እርሱ ምን ትላለህ? ዐይኖችህን ከፍቶልሃልና” አሉት፤ እርሱም፥ “ነቢይ ነው” አላቸው።