ዮሐንስ 8:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ለራሴ ክብርን አልሻም፤ የሚሻ፥ የሚፈርድም አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ የራሴን ክብር አልፈልግም፤ የሚፈልግ ግን አለ፤ ፈራጁም እርሱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ግን የእራሴን ክብር አልፈልግም፤ የሚፈልግ የሚፈርድም አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ እኔ የራሴን ክብር አልፈልግም፤ የእኔን መከበር የሚፈልግና የሚፈርድ ሌላ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ግን የራሴን ክብር አልፈልግም፤ የሚፈልግ የሚፈርድም አለ። |
እኔ በአብ ዘንድ የምከስሳችሁ አይምሰላችሁ፤ የሚከስሳችሁስ አለ፤ እርሱም እናንተ ተስፋ የምታደርጉት ሙሴ ነው።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እኔ ራሴን ባከብር ክብሬ ምንም አይጠቅመኝም፤ የሚያከብረኝስ እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ አለ።