ታዳጊህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሕይወቱን የሚያስጨንቃትን፥ በአሕዛብ የተጠላውን የአለቆችን ባርያ ቀድሱት፤ ነገሥታት ያዩታል፤ አለቆችም ስለ እግዚአብሔር ብለው ተነሥተው ይሰግዱለታል፤ የእስራኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መርጨሃለሁና።”
ዮሐንስ 8:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድም፥ “አንተ ሳምራዊ እንደ ሆንህ፥ ጋኔንም እንደ አለብህ መናገራችን በሚገባ አይደለምን?” ብለው ጠየቁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይሁድም መልሰው፣ “አንተ ሳምራዊ ነህ፤ ደግሞም ጋኔን ዐድሮብሃል ማለታችን ትክክል አይደለምን?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይሁድ መልሰው “ሳምራዊ እንደሆንህ ጋኔንም እንዳለብህ በመናገራችን ትክክል አይደለንምን?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አይሁድ “አንተ ሳምራዊ ነህ፤ ጋኔንም አለብህ፤ ማለታችን ልክ አይደለምን?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይሁድ መልሰው፦ “ሳምራዊ እንደ ሆንህ ጋኔንም እንዳለብህ በማለታችን እኛ መልካም እንል የለምን?” አሉት። |
ታዳጊህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሕይወቱን የሚያስጨንቃትን፥ በአሕዛብ የተጠላውን የአለቆችን ባርያ ቀድሱት፤ ነገሥታት ያዩታል፤ አለቆችም ስለ እግዚአብሔር ብለው ተነሥተው ይሰግዱለታል፤ የእስራኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መርጨሃለሁና።”
መልኩም የተናቀ፥ ከሰውም ልጆች ሁሉ የተዋረደ፥ የተገረፈ ሰው፥ መከራንም የተቀበለ ነው፤ ፊቱንም መልሶአልና አቃለሉት፥ አላከበሩትምም።
ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!
አይሁድ፥ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ይጠይቁት ዘንድ ካህናትንና ሌዋውያንን ከኢየሩሳሌም በላኩ ጊዜ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።
ያቺ የሰማርያ ሴትም፥ “አንተ አይሁዳዊ ስትሆን፥ እኔም ሳምራዊት ስሆን እንዴት ከእኔ ዘንድ ውኃ ልትጠጣ ትለምናለህ?” አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር በሥርዐት አይተባበሩም ነበርና።
አይሁድም እንዲህ አሉት፥ “አሁን ጋኔን እንዳለብህ ዐወቅን፤ አብርሃም ስንኳ ሞቶአል፤ ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን ቃሌን የሚጠብቅ ለዘለዓለም ሞትን አይቀምስም ትላለህ።