ብዙ ጊዜ መላልሰው በጠየቁት ጊዜም ዐይኖቹን አንሥቶ፥ “ከእናንተ ኀጢኣት የሌለበት አስቀድሞ ድንጋይ ይጣልባት” አላቸው።
ዮሐንስ 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም ቀና ብሎ ወደ እርስዋ ተመለከተና እንዲህ አላት፥ “አንቺ ሴት፥ የሚከሱሽ ወዴት አሉ?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም ቀና ብሎ፣ “አንቺ ሴት፣ ሰዎቹ የት ሄዱ? የፈረደብሽ የለምን?” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም ቀና ብሎ “አንቺ ሴት! ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን?” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ቀና ብሎ፥ “አንቺ ሴት ከሳሾችሽ የት አሉ? የፈረደብሽ ማንም የለምን?” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ፦ “አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን?” አላት። |
ብዙ ጊዜ መላልሰው በጠየቁት ጊዜም ዐይኖቹን አንሥቶ፥ “ከእናንተ ኀጢኣት የሌለበት አስቀድሞ ድንጋይ ይጣልባት” አላቸው።
እነርሱ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ኅሊናቸው ወቅሶአቸው ከሽማግሌዎች ጀምሮ እስከ ኋለኞቹ ድረስ፥ አንዳንድ እያሉ ወጡ፤ ጌታችን ኢየሱስም ብቻውን ቀረ፤ ሴትዮዪቱም በመካከል ቆማ ነበር።