ዮሐንስ 7:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቹ ለበዓል ከወጡ በኋላ፥ እርሱም ያንጊዜ በግልጥ ሳይሆን ተሰውሮ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ፣ ወንድሞቹ ወደ በዓሉ ከሄዱ በኋላ፣ እርሱም በግልጽ ሳይሆን በስውር ወደ በዓሉ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞቹ ግን ወደ በዓሉ ከወጡ በኋላ፥ እርሱ ደግሞ በግልጥ ሳይሆን ተሰውሮ ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ወንድሞቹ ወደ በዓሉ ከሄዱ በኋላ እርሱ በይፋ ሳይሆን በስውር ወደ በዓሉ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞቹ ግን ወደ በዓሉ ከወጡ በኋላ በዚያን ጊዜ እርሱ ደግሞ በግልጥ ሳይሆን ተሰውሮ ወጣ። |
ከዚያም ወዲያ ጌታችን ኢየሱስ በአይሁድ መካከል በግልጥ አልተመላለሰም፤ ነገር ግን ለምድረ በዳ አቅራቢያ ወደ ሆነች ምድር፥ ኤፍሬም ወደምትባል ከተማ ሄደ፤ በዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጠ።
ወንድሞቹም ጌታችን ኢየሱስን እንዲህ አሉት- “ደቀ መዛሙርትህ የምትሠራውን ሥራህን እንዲያዩ ከዚህ ወጥተህ ወደ ይሁዳ ሀገር ሂድ።