ዮሐንስ 6:65 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አላቸው፥ “ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ከአብ ካልተሰጠው በቀር ወደ እኔ መምጣት የሚቻለው የለም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም፣ “ ‘ከአብ ካልተሰጠው በቀር፣ ማንም ወደ እኔ ሊመጣ አይችልም’ ያልኋችሁ ለዚህ ነው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አለ፦ “ስለዚህ አልኋችሁ፤ ከአብ የተሰጠው ካልሆነ ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፥ ያልኋችሁ በዚህ ምክንያት ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ኢየሱስ “ከአብ የተፈቀደለት ካልሆነ በቀር ወደ እኔ መምጣት የሚችል የለም ያልኳችሁ ስለዚህ ነው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ፦ ስለዚህ አልኋችሁ፥ ከአብ የተሰጠው ካልሆነ ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም አለ። |
ከዚህ ቦታ ያይደሉ ሌሎች በጎችም አሉኝ፤ እነርሱንም ወደዚህ አመጣቸው ዘንድ ይገባኛል፤ ቃሌንም ይሰሙኛል፤ ለአንድ እረኛም አንድ መንጋ ይሆናሉ።
ዮሐንስም መልሶ እንዲህ አለ፥ “ሰው ከሰማይ ካልተሰጠው በስተቀር እርሱ ራሱ ጸጋን ገንዘብ ሊያደርግ ምንም አይችልም።
ይህንም ጸጋ እግዚአብሔር ሰጥቶአችኋል፤ ነገር ግን ስለ እርሱ መከራ ልትቀበሉም ነው እንጂ ልታምኑበት ብቻ አይደለም።
ደግሞም “ምናልባት እግዚአብሔር እውነትን ያውቁ ዘንድ ንስሓን ይሰጣቸዋልና ፈቃዱን ለማድረግ በዲያብሎስ ሕያዋን ሆነው ከተያዙበት ወጥመድ ወጥተው ወደ አእምሮ ይመለሳሉ፤” ብሎ የሚቃወሙትን በየዋህነት ይቅጣ።
የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ፥ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።