ያም የንጉሥ ወገን የሆነ ሰው፥ “አቤቱ፥ ልጄ ሳይሞት ፈጥነህ ውረድ” አለው።
ሹሙም፣ “ጌታዬ፤ ልጄ ከመሞቱ በፊት እባክህ ድረስልኝ” አለው።
ሹሙም “ጌታ ሆይ! ብላቴናዬ ሳይሞት ውረድ፤” አለው።
ሹሙም “ጌታ ሆይ! ልጄ ከመሞቱ በፊት እባክህ ቶሎ ውረድ” አለው።
ሹሙም፦ ጌታ ሆይ፥ ብላቴናዬ ሳይሞት ውረድ አለው።
“ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለችና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት፤” ብሎ አጥብቆ ለመነው።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ምልክትንና ድንቅ ሥራን ካላያችሁ አታምኑም” አለው።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ሂድ፤ ልጅህስ ድኖአል” አለው፤ ያም ሰው፦ ጌታችን ኢየሱስ በነገረው ቃል አምኖ ሄደ።