ዮሐንስ 4:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም፥ “ክርስቶስ የሚሉት መሲሕ እንደሚመጣ እናውቃለን፤ እርሱም በሚመጣ ጊዜ ሁሉን ይነግረናል” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴትዮዋም፣ “ክርስቶስ የተባለ መሲሕ እንደሚመጣ ዐውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ነገር ይነግረናል” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቲቱ “ክርስቶስ የሚባል መሢሕ እንደሚመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል፤” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴትዮዋም “ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንደሚመጣ ዐውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ነገር ይነግረናል” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱ፦ ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል አለችው። |
ናትናኤልም፥ “በየት ታውቀኛለህ?” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “ገና ፊልጶስ ሳይጠራህ በበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አይችሃለሁ” አለው።
ሴቲቱንም፥ “እኛ ራሳችን ይህ በእውነት የዓለም መድኀኒት ክርስቶስ እንደ ሆነ ሰምተንና ተረድተን ነው እንጂ በአንቺ ቃል ያመንበት አይደለም” አሏት።