አብርሃምም፦ ‘ሙሴንና ነቢያትን ካልሰሙማ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ቢኖርም እንኳ አይሰሙትም፤ አያምኑትምም’ አለው።”
ዮሐንስ 20:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ አስቀድሞ ወደ መቃብሩ የደረሰው ሌላዉ ደቀ መዝሙር ገባ፤ አይቶም አመነ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አስቀድሞ ከመቃብሩ የደረሰው ሌላው ደቀ መዝሙር ወደ ውስጥ ገባ፤ አይቶም አመነ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ አስቀድሞ ወደ መቃብር የመጣውም ሌላው ደቀመዝሙር ገባ፤ አየም፤ አመነም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ያ ቀድሞ የደረሰው ደቀ መዝሙር ወደ መቃብሩ ውስጥ ገብቶ አየና አመነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ አስቀድሞ ወደ መቃብር የመጣውንም ሌላው ደቀ መዝሙር ደግሞ ገባ፥ አየም፥ አመነም፤ |
አብርሃምም፦ ‘ሙሴንና ነቢያትን ካልሰሙማ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ቢኖርም እንኳ አይሰሙትም፤ አያምኑትምም’ አለው።”
ናትናኤልም መልሶ፥ “መምህር ሆይ፥ በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ የእስራኤልም ንጉሥ አንተ ነህ” አለው።
ሌሎች ደቀ መዛሙርትም፥ “ጌታችንን አየነው” አሉት፤ እርሱ ግን፥ “የችንካሩን ምልክት በእጁ ካላየሁ፥ ጣቴንም ወደ ተቸነከረበት ካልጨመርሁ፥ እጄንም ወደ ጎኑ ካላገባሁ አላምንም” አላቸው።