ዮሐንስ 20:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማርያም ግን ከመቃብሩ በስተውጭ እያለቀሰች ቆማ ነበረ፤ እያለቀሰችም ወደ መቃብሩ ጐንበስ ብላ ተመለከተች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማርያም ግን ከመቃብሩ ውጭ ቆማ ታለቅስ ነበር፤ እያለቀሰችም መቃብሩን ለማየት ጐንበስ አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብሩ በስተ ውጭ ቆማ ነበር። እያለቀሰችም ወደ መቃብር ዝቅ ብላ ተመለከተች፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መግደላዊት ማርያም እያለቀሰች፥ ከመቃብሩ በስተውጭ ቆማ ነበር፤ እያለቀሰችም ጐንበስ ብላ ወደ መቃብሩ ውስጥ ተመለከተች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብሩ በስተ ውጭ ቆማ ነበር። ስታለቅስ ወደ መቃብር ዝቅ ብላ ተመለከተች፤ |