ፍቅራቸውና ጥላቸው ቅንአታቸውም በአንድነት እነሆ፥ ጠፍቶአል፤ ከፀሓይ በታችም በሚሠራው ነገር ሁሉ ለዘለዓለም ዕድል ፈንታ ከእንግዲህ ወዲህ የላቸውም።
ዮሐንስ 2:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አሁንም ቅዱና ወስዳችሁ ለአሳዳሪው ስጡት” አላቸው፤ ወስደውም ሰጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ከላዩ ቀድታችሁ ለድግሱ ኀላፊ ስጡት” አላቸው። እነርሱም እንዳዘዛቸው አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት፤” አላቸው፤ ሰጡትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አገልጋዮቹን፦ “በሉ አሁን ቀድታችሁ ለግብዣው ኀላፊ ስጡት” አላቸው፤ እነርሱም ወስደው ሰጡት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም። |
ፍቅራቸውና ጥላቸው ቅንአታቸውም በአንድነት እነሆ፥ ጠፍቶአል፤ ከፀሓይ በታችም በሚሠራው ነገር ሁሉ ለዘለዓለም ዕድል ፈንታ ከእንግዲህ ወዲህ የላቸውም።
አሳዳሪውም ያን የወይን ጠጅ የሆነውን ውኃ ቀምሶ አደነቀ፤ ከወዴት እንደ መጣም አላወቀም፤ የቀዱት አሳላፊዎች ግን የወይን ጠጅ የሆነውን ያን ውኃ ያውቁ ነበር። ውኃዉን የሞሉ እነርሱ ነበሩና።
ለሁሉም እንደሚገባው አድርጉ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን ስጡ፤ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ስጡ፤ ዐሥራት ለሚገባው ዐሥራትን ስጡ፤ ሊፈሩት የሚገባውን ፍሩ፤ ክብር የሚገባውንም አክብሩ።