የፋሲካም የመዘጋጀት ቀን ነበር፤ ጊዜዉም ስድስት ሰዓት ያህል ነበር፤ ጲላጦስም አይሁድን፥ “እነሆ፥ ንጉሣችሁ” አላቸው፤
ዮሐንስ 19:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊቃነ ካህናትም ጲላጦስን አሉት፥ “እርሱ ራሱ ‘እኔ የአይሁድ ንጉሥ ነኝ’ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለህ አትጻፍ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአይሁድ የካህናት አለቆች ጲላጦስን በመቃወም፣ “እርሱ፣ ‘የአይሁድ ንጉሥ ነኝ’ እንዳለ ጻፍ እንጂ ‘የአይሁድ ንጉሥ’ ብለህ አትጻፍ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን “እርሱ ‘የአይሁድ ንጉሥ ነኝ’ አለ ብለህ ጻፍ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለህ አትጻፍ፤” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን፥ “አንተ ‘የአይሁድ ንጉሥ’ ብለህ አትጻፍ፤ ነገር ግን ‘ይህ ሰው እኔ የአይሁድ ንጉሥ ነኝ’ ብሎአል ብለህ ጻፍ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን፦ “እርሱ፦ ‘የአይሁድ ንጉስ ነኝ’ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለህ አትጻፍ” አሉት። |
የፋሲካም የመዘጋጀት ቀን ነበር፤ ጊዜዉም ስድስት ሰዓት ያህል ነበር፤ ጲላጦስም አይሁድን፥ “እነሆ፥ ንጉሣችሁ” አላቸው፤