“እርስ በርሳችሁ ቷደዱ ዘንድ፥ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።
ዮሐንስ 15:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስ በርሳችሁም እንድቷደዱ ይህን አዝዣችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ፣ ትእዛዜ ይህች ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ አዛችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ እኔ የማዛችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ይህን አዛችኋለሁ። |
“እርስ በርሳችሁ ቷደዱ ዘንድ፥ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።
አሁንም እመቤት ሆይ! እርስ በርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ፤ ይህች ከመጀመሪያ በእኛ ዘንድ የነበረች ትእዛዝ ናት እንጂ አዲስ ትእዛዝን እንደምጽፍልሽ አይደለም።