ዮሐንስ 11:56 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድም ጌታችን ኢየሱስን ይፈልጉት ጀመር፤ በቤተ መቅደስም ቆመው እርስ በርሳቸው፥ “ምን ይመስላችኋል? ለበዓል አይመጣ ይሆን?” ተባባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስንም ይፈልጉት ነበር፤ በቤተ መቅደስም ቆመው፣ “ምን ይመስላችኋል? ለበዓሉ አይመጣ ይሆን?” ተባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስንም ይፈልጉት ነበር፤ በመቅደስም ቆመው እርስ በርሳቸው “ምን ይመስላችኋል? ወደ በዓሉ አይመጣም ይሆንን?” ተባባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም በቤተ መቅደስ ቆመው የኢየሱስን መምጣት ይጠባበቁ ስለ ነበር “ምን ታስባላችሁ? ወደ በዓሉ የሚመጣ አይመስላችሁምን?” እያሉ እርስ በእርሳቸው ይጠያየቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስንም ይፈልጉት ነበር፤ በመቅደስም ቆመው እርስ በርሳቸው፦ “ምን ይመስላችኋል? ወደ በዓሉ አይመጣም ይሆንን?” ተባባሉ። |