ዮሐንስ 11:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁ ብንተወውም ሁሉ ያምኑበታል፤ የሮም ሰዎችም መጥተው ሀገራችንንና ወገናችንን ይወስዱብናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁ ብንተወው ሰው ሁሉ በርሱ ያምናል፤ ሮማውያንም መጥተው ስፍራችንንና ሕዝባችንን ይወስዱብናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁ ብንተወው ሁሉም በእርሱ ያምናሉ፤ የሮሜም ሰዎች መጥተው አገራችንንና ወገናችንንም ይወስዳሉ፤” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁ ብንተወው ሰው ሁሉ በእርሱ ያምናል፤ ሮማውያንም መጥተው ቤተ መቅደሳችንንና ሕዝባችንን ሁሉ ይደመስሳሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ ብንተወው ሁሉ በእርሱ ያምናሉ፤ የሮሜም ሰዎች መጥተው አገራችንን ወገናችንንም ይወስዳሉ” አሉ። |
እናንተ ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! የጽድቅንና የዕውቀትን መክፈቻ ወስዳችሁ ትሰውራላችሁና፤ እናንተም አትገቡምና፤ የሚገቡትንም መግባትን ትከለክሉአቸዋላችሁ።”
“በኢየሱስ ስም ለማንም እንዳታስተምሩ ከልክለናችሁ አልነበረምን? እነሆ፥ ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞላችኋት፤ የዚያንም ሰው ደም በእኛ ላይ ታመጡብን ዘንድ ትሻላችሁን?” አላቸው።