ዮሐንስ 11:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ብላ ሄደች፤ እኅቷን ማርያምንም ቀስ ብላ ጠራችና፥ “እነሆ፥ መምህራችን መጥቶ ይጠራሻል” አለቻት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ካለች በኋላ፣ ተመልሳ እኅቷን ማርያምን ለብቻዋ ጠርታ፣ “መምህሩ መጥቷል፤ ይፈልግሻልም” አለቻት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንም ብላ ሄደች፤ እኅትዋንም ማርያምን በስውር ጠርታ “መምህር መጥቷል፤ እየጠራሽም ነው፤” አለቻት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማርታ ይህን ከተናገረች በኋላ ሄደችና እኅትዋን ማርያምን “መምህር መጥቶአል፤ አንቺንም ይጠራሻል” ብላ በስውር ጠራቻት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም ብላ ሄደች እኅትዋንም ማርያምን በስውር ጠርታ፦ “መምህሩ መጥቶአል ይጠራሽማል” አለቻት። |
እርሱም “ወደ ከተማ ከእገሌ ዘንድ ሄዳችሁ ‘መምህር ጊዜዬ ቀርቦአል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ከአንተ ዘንድ ፋሲካን አደርጋለሁ ይላል’ በሉት፤” አለ።
ከዮሐንስ ዘንድ ሰምተው ጌታችን ኢየሱስን ከተከተሉት ከሁለቱም አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበር።
ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ቃሉን ይሰሙታል፤ እርሱም በጎቹን በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ አውጥቶም ያሰማራቸዋል።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ማርያም!” አላት፤ እርስዋም መለስ ብላ በዕብራይስጥ ቋንቋ፥ “ረቡኒ!” አለችው፤ ትርጓሜዉም “መምህር” ማለት ነው።
ጌታችን ኢየሱስ ይወደው የነበረ ያ ደቀ መዝሙርም ለጴጥሮስ፥ “ጌታችን ነው እኮ” አለው፤ ስምዖን ጴጥሮስም ጌታችን እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ የሚለብሰውን ልብስ አንሥቶ በወገቡ ታጠቀ፤ ራቁቱን ነበርና ወደ ባሕር ተወረወረ።