ዳግመኛም ሊይዙት ፈለጉ፤ ከእጃቸውም አመለጠ።
እንደ ገናም ሊይዙት ሞከሩ፤ እርሱ ግን ከእጃቸው አመለጠ።
ደግመኛም ሊይዙት ፈለጉ፤ ከእጃቸውም አምልጦ ሄደ።
እነርሱም እንደገና ሊይዙት ፈለጉ፤ እርሱ ግን ከእጃቸው አምልጦ ሄደ።
እንግዲህ ደግመው ሊይዙት ፈለጉ፤ ከእጃቸውም ወጣ።
ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት።
ዳግመኛም አይሁድ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ።
ስለዚህም ሊይዙት ወደው ነበር፤ ነገር ግን እጁን በእርሱ ላይ ያነሣ የለም፤ ጊዜዉ ገና አልደረሰም ነበርና።
ከእነርሱም ሊይዙት የወደዱ ነበሩ፤ ነገር ግን በእርሱ ላይ እጁን ያነሣ የለም።
ሊደበድቡትም ድንጋይ አነሡ፤ ጌታችን ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው፤ ከቤተ መቅደስም ወጣ፤ በመካከላቸውም አልፎ ሄደ።