La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 1:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ምስ​ክሩ ዮሐ​ንስ ስለ እርሱ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ተና​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እኔ ስለ እርሱ ከእኔ በፊት የነ​በረ ከእኔ በኋላ ይመ​ጣል ያል​ኋ​ችሁ ሰው ይህ ነው፥ እርሱ ከእኔ አስ​ቀ​ድሞ ነበ​ረና።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዮሐንስም፣ “ ‘ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለ ነበረ ከእኔ ይልቃል’ ብዬ የመሰከርሁለት እርሱ ነው” በማለት ጮኾ ስለ እርሱ መሰከረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ፤ እንዲህም ብሎ ጮኸ “‘ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል፤’ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነበረ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዮሐንስም “ ‘ያ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለነበረ ከእኔ እጅግ ይበልጣል’ ብዬ የነገርኳችሁ እነሆ፥ ይህ ነው” እያለ መሰከረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ እንዲህም ብሎ ጮኸ፦ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል፤ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነበረ።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 1:15
21 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ለሥራው የመንገዱ መጀመሪያ አድርጎ ፈጠረኝ፥


ሕፃን ተወ​ል​ዶ​ል​ና​ልና፥ ወንድ ልጅም ተሰ​ጥ​ቶ​ና​ልና፤ አለ​ቅ​ነ​ትም በጫ​ን​ቃው ላይ ይሆ​ናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አም​ላክ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም አባት፥ የሰ​ላም አለቃ ተብሎ ይጠ​ራል፤


አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።


እኔስ “ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤


“ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል።


ዮሐ​ን​ስም መልሶ ሁሉ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ በውኃ አጠ​ም​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ግን የሚ​በ​ል​ጠኝ የጫ​ማ​ውን ማሰ​ሪያ እንኳ ልፈ​ታ​ለት የማ​ይ​ገ​ባኝ ይመ​ጣል፤ እርሱ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ በእ​ሳ​ትም ያጠ​ም​ቃ​ች​ኋል።


ከእኔ በኋላ የሚ​መ​ጣው፥ ከእኔ በፊት የነ​በ​ረው፥ የጫ​ማ​ውን ጠፍር ልፈታ እንኳ የማ​ይ​ገ​ባኝ ነው።”


አሁ​ንም አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር ከአ​ንተ ጋር በነ​በ​ረኝ ክብር በአ​ንተ ዘንድ አክ​ብ​ረኝ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ አብ​ር​ሃም ሳይ​ወ​ለድ እኔ አለሁ።” አላ​ቸው።


እርሱ ከሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ነበረ፤ ሁሉም በእ​ርሱ ጸና።


ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ትና​ን​ት​ናና ዛሬ እስከ ዘለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር እርሱ ነውና።


እንዲሁም “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊላደልፊያም ወደ ሎዲቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ፤” አለኝ።


“በሰምርኔስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ ሞቶ የነበረው ሕያውም የሆነው ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል፦