ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል፤ ከእስራኤልም የቀሩትን ይሰበስባል፤ ከይሁዳም የተበተኑትን ከአራቱ የምድር ማዕዘኖች ያከማቻል።
ኢዩኤል 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ እነርሱን ከሸጣችሁበት ስፍራ አስነሣቸዋለሁ፤ ብድራታችሁንም በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነሆ፤ እነርሱን ከሸጣችሁባቸው ቦታዎች አነሣሣቸዋለሁ፤ እናንተም ያደረጋችሁትን በገዛ ራሳችሁ ላይ እመልስባችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ እነርሱን ከሸጣችሁበት ስፍራ አስነሣቸዋለሁ፥ በደሉን በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ አሁን ከተሸጡባቸው ስፍራዎች አነሣሥቼ እንዲወጡ አደርጋለሁ፤ በእነርሱ ላይ የፈጸማችሁትን በደል ሁሉ በእናንተ ላይ መልሼ አመጣባችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ እነርሱን ከሸጣችሁበት ስፍራ አስነሣቸዋለሁ፥ ብድራታችሁንም በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ። |
ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል፤ ከእስራኤልም የቀሩትን ይሰበስባል፤ ከይሁዳም የተበተኑትን ከአራቱ የምድር ማዕዘኖች ያከማቻል።
ነገር ግን፥ “የእስራኤልን ቤት ዘር ከሰሜን ሀገርና ካሳደዷቸውም ሀገር ሁሉ ያወጣና የመራ ሕያው እግዚአብሔርን!” ይባላል፤ በምድራቸውም መልሶ ያኖራቸዋል።
“እነሆ አንተን ከሩቅ፥ ዘርህንም ከምርኮ ሀገር አድናለሁና ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ! አትፍራ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ አንተም እስራኤል ሆይ! አትደንግጥ፤ ያዕቆብም ይመለሳል፤ ያርፍማል፤ ተዘልሎም ይቀመጣል፤ ማንም አያስፈራውም።
ስለዚህ የሚበሉህ ሁሉ ይበላሉ፤ የሚማርኩህም ሁላቸው ይማረካሉ፤ የዘረፉህም ይዘረፋሉ፤ የሚማርኩህንም ሁሉ ለመማረክ አሳልፌ እሰጣለሁ።
እነሆ፥ ከሰሜን ሀገር አመጣቸዋለሁ፤ ከምድርም ዳርቻ ለበዓለ ፋሲካ እሰበስባቸዋለሁ፤ ብዙ አሕዛብም ይወለዳሉ፤ ወደዚህም ይመለሳሉ።
እነሆ በቍጣዬና በመዓቴ፥ በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት ሀገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ ተዘልለውም እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤
ከአሕዛብም መካከል አወጣችኋለሁ፤ ከየሀገሩም ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፤ ወደ ገዛ ምድራችሁም እመልሳችኋለሁ።
ከብዙ ዘመንም በኋላ ትፈለጋለህ፤ በኋለኛውም ዘመን፥ የዘለዓለም ባድማ በነበሩ በእስራኤል ተራሮች ላይ ከብዙ ሕዝብ ውስጥ ወደ ተሰበሰበች፥ ከሰይፍ ወደ ተመለሰች ምድር ትገባለህ፤ እርስዋም ከሕዝብ ውስጥ ወጥታለች፤ ሁሉም በሰላም ይቀመጡበታል።
“ጢሮስና ሲዶና የፍልስጥኤም አውራጃ ገሊላም ሁሉ ሆይ! ከእናንተ ጋራ ምን አለኝ? እናንተ በቀልን ትበቀሉኛላችሁን? ቂምንስ ትቀየሙኛላችሁን? ፈጥኜ በችኰላ ፍዳን በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።
ይሁዳን ለእኔ ገትሬአለሁ፣ ቀስቱን በኤፍሬም ሞልቼአለሁ፣ ጽዮን ሆይ፥ ልጆችሽን በግሪክ ልጆች ላይ አስነሣለሁ፥ አንቺንም እንደ ኃያል ሰው ሰይፍ አደርግሻለሁ።
ጌታ ኢየሱስ ከኀያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።
ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት በዚህ ነው።
አዶኒቤዜቅም፥ “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡ ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ በታች ፍርፋሪ ይለቅሙ ነበሩ፤ እኔ እንዳደረግሁ እግዚአብሔር እንዲሁ መለሰልኝ” አለ። ወደ ኢየሩሳሌምም ወሰዱት፥ በዚያም ሞተ።
ሳሙኤልም አጋግን፥ “ሰይፍህ ሴቶችን ልጆች አልባ እንዳደረገቻቸው እንዲሁ እናትህ በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች” አለ፥ ሳሙኤልም አጋግን በእግዚአብሔር ፊት በጌልጌላ ወጋው።