ብትሄድ ግን፥ በእነርሱም ማሸነፍን ብታስብ፥ የማጽናትና የመጣል ኀይል ከእግዚአብሔር ዘንድ ነውና እግዚአብሔር በጠላቶችህ ፊት ይጥልሃል” አለው።
ኢዩኤል 3:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማረሻችሁን ሰይፍ፥ ማጭዳችሁንም ጦር ለማድረግ ቀጥቅጡ፤ ደካማውም፦ እኔ ብርቱ ነኝ ይበል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማረሻችሁ ሰይፍ፣ ማጭዳችሁም ጦር እንዲሆን ቀጥቅጡት፤ ደካማውም ሰው፣ “እኔ ብርቱ ነኝ” ይበል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማረሻችሁን ሰይፍ፥ ማጭዳችሁንም ጦር ለማድረግ ቀጥቅጡ፥ ደካማውም፦ እኔ ብርቱ ነኛ ይበል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማረሻችሁ ሰይፍ፥ ማጭዳችሁም ጦር እንዲሆን ቀጥቅጡ፤ ደካማውም እንኳ ‘እኔ ብርቱ ነኝ’ ይበል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማረሻችሁን ሰይፍ፥ ማጭዳችሁንም ጦር ለማድረግ ቀጥቅጡ፥ ደካማውም፦ እኔ ብርቱ ነኛ ይበል። |
ብትሄድ ግን፥ በእነርሱም ማሸነፍን ብታስብ፥ የማጽናትና የመጣል ኀይል ከእግዚአብሔር ዘንድ ነውና እግዚአብሔር በጠላቶችህ ፊት ይጥልሃል” አለው።
በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፤ ብዙ አሕዛብንም ይዘልፋቸዋል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ፥ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍን አያነሣም፤ ሰልፍንም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም።
“ፍላጾችን አዘጋጁ፤ ጕራንጕሬዎችንም ሙሉ፤ እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ ቍጣው በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ንጉሥ መንፈስ አስነሥቶአል፤ የእግዚአብሔር በቀል የመቅደሱ በቀል ነውና።
በብዙዎችም አሕዛብ መካከል ይፈርዳል፥ በሩቅም ባሉ በብርቱዎች አሕዛብ ላይ ይበይናል፥ ሰይፋቸውንም ማረሻ፥ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፥ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም ከእንግዲህም ወዲህ ሰልፍ አይማሩም።
በዚያ ቀን እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ይመክትላቸዋል፣ በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት ይሆናል፣ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ አምላክ ይሆናል።
እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “አሁን ግን ኮሮጆ ያለው ኮሮጆውን ይያዝ፤ ከረጢትም ያለው እንዲሁ ያድርግ፤ ሰይፍ የሌለውም ልብሱን ሸጦ ሰይፍ ይግዛ።