ኢዮብ 8:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤቱን ቢደግፈውም አይቆምለትም፤ የጀመረውንም አይፈጽምም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድሩ ላይ ቢደገፍ ይበጠስበታል፤ አጥብቆም ቢይዘው አይጸናም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤቱን ይደገፈዋል፥ ነገር ግን አይቆምለትም፥ ይይዘውማል፥ አይጸናለትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሸረሪቱ ድር ላይ ቢደገፍ ጸንቶ አይቆምም፤ የሸረሪት ድሩን ቢጨብጥ ይበጠስበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤቱን ይደግፈዋል፥ አይቆምለትም፥ ይይዘውማል፥ አይጸናለትም። |
እኔ አስወጣዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ወደ ሚሰርቀውም ቤት፥ በሐሰትም በስሜ ወደሚምለው ቤት ይገባል፣ በቤቱም ውስጥ ይኖራል፥ እርሱንም፥ እንጨቱንና ድንጋዩን፥ ይበላል።