ቤቱም ያለ ነዋሪ ይቀራል፥ ማደሪያውም የሸረሪት ድር ይሆናል።
መተማመኛው ቀጭን ክር፣ ድጋፉም የሸረሪት ድር ነው።
ተስፋው ይቈረጣል፥ መተማመኛው እንደ ሸረሪት ቤት ይሆናል።
እንደ ሸረሪት ድር በሚበጠስ ነገር ይታመናሉ፤ ተስፋ የሚያደርጉበት ነገር እንኳ ቢኖር በቀላሉ ይጠፋል።
ተስፋው ይቈረጣል፥ እምነቱም እንደ ሸረሪት ቤት ይሆናል።
ጻድቅ ሰው በሞተ ጊዜ ተስፋውን አያጣም፥ የክፉዎች ትምክሕታቸው ግን ትጠፋለች።
በከንቱ ነገር ደስ የሚላችሁ በኀይላችን ቀንዶችን አበቀልን የምትሉ አይደለምን?