La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 5:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የም​ድረ በዳ አራ​ዊ​ትም ከአ​ንተ ጋር ይስ​ማ​ማሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከሜዳ ድንጋዮች ጋራ ትዋዋላለህና፤ የዱር አራዊትም ከአንተ ጋራ ይስማማሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ቃል ኪዳንህ ከምድረበዳ ድንጋይ ጋር ይሆናልና፥ የምድረ በዳም አራዊት ከአንተ ጋር ይስማማሉና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በምታርሰው መሬት ላይ ድንጋይ አያውክህም፤ ከአራዊትም ጋር በሰላም ትኖራለህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ቃል ኪዳንህ ከምድረ በዳ ድንጋይ ጋር ይሆናልና፥ የምድረ በዳም አራዊት ከአንተ ጋር ይስማማሉና።

Ver Capítulo



ኢዮብ 5:23
10 Referencias Cruzadas  

ያን​ጊዜ ተኵ​ላና በግ በአ​ን​ድ​ነት ይሰ​ማ​ራሉ፤ አን​በ​ሳም እንደ በሬ ገለባ ይበ​ላል፤ የእ​ባ​ብም መብል ትቢያ ይሆ​ናል። በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራዬ ሁሉ አይ​ጐ​ዱም፤ አያ​ጠ​ፉ​ምም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“የሰ​ላ​ም​ንም ቃል ኪዳን ከዳ​ዊት ቤት ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ክፉ​ዎ​ች​ንም አራ​ዊት ከም​ድር አጠ​ፋ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለ​ውም በም​ድረ በዳ ይኖ​ራሉ፤ በዱ​ርም ውስጥ ይተ​ኛሉ።


የም​ድረ በዳ ዛፍም ፍሬ​ውን ይሰ​ጣል፤ ምድ​ርም ቡቃ​ያ​ዋን ትሰ​ጣ​ለች፤ በም​ድ​ራ​ቸ​ውም በሰ​ላም ታም​ነው ይኖ​ራሉ፤ የቀ​ን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም ማነቆ በሰ​በ​ርሁ ጊዜ፥ ከሚ​ገ​ዙ​አ​ቸ​ውም እጅ ባዳ​ን​ኋ​ቸው ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


በዚ​ያም ቀን ከም​ድር አራ​ዊ​ትና ከሰ​ማይ ወፎች፥ ከመ​ሬ​ትም ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ጋር ቃል ኪዳን አደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ። ቀስ​ት​ንና ሰይ​ፍን፥ ጦር​ንም ከም​ድሩ እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለ​ሽም ትቀ​መ​ጫ​ለሽ።


በም​ድ​ራ​ች​ሁም ላይ ሰላ​ምን እሰ​ጣ​ለሁ፤ ትተ​ኛ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ች​ሁም የለም፤ ክፉ​ዎ​ች​ንም አራ​ዊት ከም​ድ​ራ​ችሁ አጠ​ፋ​ለሁ።