ኢዮብ 38:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በውኑ የሰባቱን ከዋክብት ዘለላ ታስር ዘንድ፥ ወይስ ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ ትፈታ ዘንድ ትችላለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ፕልያዲስ የተባሉትን ውብ ከዋክብት ልትለጕም፣ ወይም የኦርዮንን ማሰሪያ ልትፈታ ትችላለህን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ የሰባቱን ከዋክብት ዘለላ ታስር ዘንድ፥ ወይስ ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ ትፈታ ዘንድ ትችላለህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘ፕልያዲስ’ የተባሉትን ከዋክብት በአንድነት ማሰር ትችላለህን? ኦርዮን የተባሉትንስ ከዋክብት የተያያዙበትን ገመድ መበጠስ ትችላለህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ የሰባቱን ከዋክብት ዘለላ ታስር ዘንድ፥ ወይስ ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ ትፈታ ዘንድ ትችላለህን? |
ወይስ ማዛሮት የሚባሉትን ከዋክብት በጊዜያቸው ታወጣ ዘንድ፥ ወይስ የምሽቱን ኮከብ ከልጆቹ ጋር ትመራ ዘንድ ትችላለህን?
ድብ የሚባለውን ኮከብና ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ፥ የአጥቢያ ከዋክብትንም፥ በአዜብም በኩል ያሉትን የከዋክብት ማደሪያዎች ፈጥሮአል።
ሁሉን የሚሠራና የሚያቅናና፥ ብርሃኑን ወደ መስዕ የሚመልሰው፥ ቀኑን እንደ ሌሊት የሚያጨልመው፥ የባሕሩንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት የሚያፈስሰው ስሙ ሁሉን የሚችል ጌታ እግዚአብሔር ነው።