ኢዮብ 37:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን የቍጣውን ድምፅ ስማ፥ ከአፉም የሚወጣውን ጕርምርምታ አድምጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስሙ! የድምፁን ጩኸት፣ ከአፉም የሚወጣውን ጕርምርምታ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የድምፁን መትመም ስሙ፥ ከአፉም የሚወጣውን ጉርምርምታ አድምጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአፉ የሚወጣውን ድምፅ ስሙ እንደ ነጐድጓድ የሚያጒረመርመውን ቃሉን አድምጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የድምፁን መትመም ስሙ፥ ከአፉም የሚወጣውን ጕርምርምታ አድምጡ። |
ኀያሉ እግዚአብሔር በድምፁ ድንቅ አድርጎ ያንጐደጕዳል፤ ለእንስሳት በየጊዜው ምግባቸውን ያዘጋጃል፥ የሚተኙበትንም ጊዜ ያውቃሉ፤ በዚህ ሁሉ ልብህ አይደንግጥብህ፤ ሥጋህም ልብህም ከግዘፉ አይለወጥብህ፤ እርሱም እኛ የማናውቀውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።
ድምፁን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰማይ ይታወካሉ፤ ከምድርም ዳር ደመናትን ያወጣል፤ ለዝናብም ጊዜ መብረቅን ያደርጋል፤ ነፋስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።