ሰው ከእግዚአብሔር ጕብኝት ሲኖረው እግዚአብሔር አይጐበኘውም አትበል።
‘እግዚአብሔርን ለማስደሰት መሞከር፣ ለሰው አንዳች አይጠቅምም’ ብሏልና።
‘እግዚአብሔርን ማስደሰት፥ ለሰው ምንም አይጠቅመውም’ ይላል።
ኀጢአተኛውን ክፉ ቀን ትጠብቀዋለች፤ በቍጣ ቀንም ይወስዱታል።
እግዚአብሔር ምን ያደርገናል? ሁሉን የሚችል አምላክስ ምን ያመጣብናል? ይላሉ።
አንተ በሥራህ ንጹሕ ከሆንህ እግዚአብሔርን ምን ያገደዋል? መንገድህንስ ብታቀና ምን ይጠቅመዋል?
በእርሱ ዘንድስ ባለሟልነትን ያገኛልን? እግዚአብሔርንስ በጠራ ጊዜ ይመልስለታልን?
ኀጢአት ብሠራስ ምን አደርጋለሁ? ትላለህ።
ኀጢአቴ ከራሴ ጠጕር በዝቷልና፥ እንደ ከባድ ሸክምም በላዬ ከብዶአልና።
አቤቱ፥ በውዴታህ ጽዮንን አሰማምራት፤ የኢየሩሳሌምም ቅጽሮች ይታነጹ።
አንተ ባሕርን በኀይልህ አጸናሃት፤ አንተ የእባቡን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበርህ።
“ስለ ምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅኸንም?” ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።
እናንተም፦ እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፣ ትእዛዙንስ በመጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ፊት ኀዘንተኞች ሆነን በመሄድ ምን ይረባናል?