ኢዮብ 25:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሌቦች ዕረፍትን የሚሰጥ እንዳለ የሚመስለው አይኑር። የክፋቱስ ወጥመድ የማይመጣበት ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰራዊቱ ሊቈጠር ይችላልን? ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ለሠራዊቱ ቍጥር ስፍር አለውን? ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊቱ ብዛት ሊቈጠር ይቻላልን? የእርሱ ብርሃንስ የማያበራለት ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ለሠራዊቶቹ ቍጥር አላቸውን? ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው? |
ዐይናችሁን ወደ ሰማይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ ይህን ሁሉ የፈጠረ ማን ነው? ከዋክብትንም በሙሉ የሚቈጥራቸው እርሱ ነው፤ በየጊዜያቸው ያመጣቸዋል፤ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ በክብሩ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።
በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፤ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።
አየሁም፤ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፤