ኢዮብ 24:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በካፊያና ከተራሮች በሚወርድ ጠል ይረጥባሉ፤ መጠጊያም የላቸውምና ቋጥኙን ተተገኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተራራ በሚወርድ ዝናብ በስብሰዋል፤ መጠለያ ዐጥተው ቋጥኝ ዐቅፈዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተራሮች በሚወርድ ዝናብ ይረጥባሉ፥ መጠጊያም አጥተው ቋጥኙን ያቅፋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተራራ ላይ በሚዘንበው ዝናብ ሰውነታቸው ይረሰርሳል፤ መጠለያም አጥተው ቋጥኝ ተጠግተው ያድራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተራሮች በሚወርድ ዝናብ ይረጥባሉ፥ መጠጊያም አጥተው ቋጥኙን ያቅፋሉ። |
እኔ ተኝቼ ነበር፥ ልቤ ግን ነቅታ ነበር፤ ልጅ ወንድሜ ቃል ደጅ እየመታ መጣ፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደምደሚያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቍንዳላዬም የሌሊት ነጠብጣብ ሞልቶበታልና ክፈችልኝ።