“የእግዚአብሔርን ፍለጋ ልትመረምር ትችላለህን? ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክ ወደ ፈጠረው ፍጥረት ፍጻሜ ትደርሳለህን?
ኢዮብ 22:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ልዑል የወደደውን ያደርግ ዘንድ የሚገባው አይደለምን? ትዕቢተኞችንስ አያዋርዳቸውምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር ከፍ ባለው ሰማይ የሚኖር አይደለምን? በሩቅ ከፍታ ያሉትን ከዋክብት ያያል! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እግዚአብሔር በላይ በሰማያት አይደለምን? ከዋክብትም እንዴት ከፍ ባለ ስፍራ ላይ እንዳሉ ተመልከት።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ከፍ ባለው ሰማይ የሚኖር አይደለምን? ከዋክብት ምንም እንኳ ከፍ ባለ ስፍራ ቢሆኑ፥ እርሱ ከበላያቸው ሆኖ ይመለከታቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በሰማያት ከፍ ከፍ አይልምን? ከዋክብትም እንዴት ከፍ ከፍ እንዳሉ ተመልከት። |
“የእግዚአብሔርን ፍለጋ ልትመረምር ትችላለህን? ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክ ወደ ፈጠረው ፍጥረት ፍጻሜ ትደርሳለህን?
ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትሄድበት ጊዜ እግርህን ጠብቅ፤ የጠቢባንንም ትምህርት ለመስማት ቅረብ፤ ዳግመኛም ከሰነፎች ስጦታ መሥዋዕት አድርገህ ከመቀበል ተጠበቅ፤ እነርሱ መልካም ለመሥራት ዐዋቂዎች አይደሉምና።
እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኩል፤ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ይሁን።
ለዘለዓለም በአርያም የሚኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱሳን የሆነ፥ በቅዱሳን አድሮ የሚኖር፥ ለተዋረዱት ትዕግሥትን የሚሰጥ፥ ልባቸውም ለተቀጠቀጠ ሕይወትን የሚሰጥ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድን ነው?