ኢዮብ 10:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ ሁሉ በአንተ ዘንድ አለ። ሁሉን ነገር ማድረግ እንደምትችል፥ የሚሳንህም እንደ ሌለ አውቃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህን ሁሉ ግን በልብህ ሸሸግህ፤ ነገሩ በሐሳብህ እንደ ነበር ዐውቃለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህንም ነገሮች በልብህ ውስጥ ሰወርህ፥ ይህ ሁሉ በአሳብህ እንዳለ አውቃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለካስ እነዚህን ነገሮች በልብህ ሰውረኻቸው ኖሮአል፤ ዓላማህም ይህ እንደ ሆነ ዐወቅሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህንም ነገሮች በልብህ ውስጥ ሰወርህ፥ ይህ ሁሉ በአሳብህ እንዳለ አውቃለሁ። |
ብርሃንን ፈጠርሁ፤ ጨለማውንም ፈጠርሁ፤ ሰላምንም አደርጋለሁ፤ ክፋትንም አመጣለሁ፤ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።
የእግዚአብሔር ባለጠግነት፥ ጥበብና ዕውቀት እንዴት ጥልቅ ነው! ለመንገዱም ፍለጋ የለውም፤ ፍርዱንም የሚያውቀው የለም።
እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገድላለሁ፤ አድንማለሁ፤ እኔ እገርፋለሁ፤ ይቅርም እላለሁ፤ ከእጄም የሚያመልጥ የለም።