ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በእግዚአብሔር መካከል ለይታለች፤ ይቅርም እንዳይላችሁ ኀጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።
ኤርምያስ 5:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደላችሁም እነዚህን አስቀርታለች፤ ኀጢአታችሁም መልካምን ነገር ከእናንተ አርቃለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በደላችሁ እነዚህን አስቀርቶባችኋል። ኀጢአታችሁ መልካሙን ነገር ከልክሏችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደላችሁ እነዚህን አስቀርታለች፥ ኃጢአታችሁም መልካምን ነገር ከለከለቻችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደላችሁ በረከትን አሳጣችሁ፤ የኃጢአታችሁም ብዛት መልካም ነገር እንዳታገኙ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደላችሁ እነዚህን አስቀርታለች፥ ኃጢአታችሁም መልካምን ነገር ከለከለቻችሁ። |
ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በእግዚአብሔር መካከል ለይታለች፤ ይቅርም እንዳይላችሁ ኀጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።
አቤቱ! ኀጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኀጢአት ሠርተናልና ኀጢአታችን ተቃውሞናል፤ ነገር ግን ስለ ስምህ ብለህ አድርግ።
ለጕስቍልናሽ ከብዙዎች እረኞች ጋር ኖርሽ የአመንዝራም ሴት ፊት ነበረብሽ፥ በሁሉም ዘንድ ያለ ኀፍረት ሄድሽ። ስለዚህ የመከርና የበልግ ዝናም ተከለከለ።
ታው። የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፥ በደልሽ ተፈጸመ፤ ከእንግዲህ ወዲህ አያስማርክሽም። የኤዶምያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ በደልሽን ይጐበኘዋል፤ ኀጢአትሽንም ይገልጣል።