የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤትንና እርሻን የወይን ቦታንም እንደ ገና ይገዛሉ።”
ኤርምያስ 32:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተም፦ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ያለች ባድማ ናት፤ ለከለዳውያንም እጅ ተሰጥታለች በምትሉአት ምድር እርሻን እንደ ገና ይገዛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም፣ “ለባቢሎናውያን ዐልፋ ስለ ተሰጠች፣ ሰውና እንስሳ የማይኖሩባት ባድማ ናት” ባላችኋት በዚህች ምድር እንደ ገና መሬት ይገዛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም፦ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ያለች ባድማ ናት፥ ለከለዳውያንም እጅ ተሰጥታለች በምትሉአት ምድር እርሻን ይገዛሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ምድሪቱ ለባቢሎናውያን ስለ ተሰጠች ሰዎችም ሆኑ እንስሶች የማይኖሩባት ባድማ ትሆናለች’ ባላችኋት በዚህች ምድር የእርሻ መሬት መግዛትና መሸጥ እንደገና ይጀመራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም፦ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ያለች ባድማ ናት፥ ለከለዳውያንም እጅ ተሰጥታለች በምትሉአት ምድር እርሻን ይገዛሉ። |
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤትንና እርሻን የወይን ቦታንም እንደ ገና ይገዛሉ።”
አንተም ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እርሻውን በብር ግዛ፤ ምስክሮችንም ጥራ አልኸኝ፤ እኔም ውሉን ጽፌ አተምሁ፤ ምስክሮችንም አቆምሁ፤ ከተማዪቱ ግን ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች።”
አሁን እንግዲህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር አንተ ስለ እርስዋ፥ “በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ትሰጣለች ስለምትላት ከተማ እንዲህ ይላል፦
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናንተ፦ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ያለች ባድማ ናት በምትሉአት በዚች ስፍራ፥ የሚቀመጥባቸው በሌለ፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባድማ በሆኑ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ፥
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ባድማ ሆኖ፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባለው በዚህ ስፍራ በከተሞችም ሁሉ መንጎቻቸውን የሚያሳርፉበት የእረኞች መኖሪያ ይሆናል።
ተዘልለውም ይቀመጡባታል፤ ቤቶችንም ይሠራሉ፤ ወይኑንም ይተክላሉ፤ በዙሪያቸውም በአሉ በሚንቋቸው ሁሉ ላይ ፍርድን በአደረግሁ ጊዜ ተዘልለው ይቀመጣሉ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካቸው፥ የአባቶቻቸውም አምላክ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።