ደግሞም በይሁዳ ተራሮች ላይ መስገጃዎችን ሠራ፤ በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን እንዲያመነዝሩ አደረጋቸው፤ የይሁዳንም ሰዎች አሳታቸው።
ኤርምያስ 3:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዳተኛዪቱም እስራኤል እንዳመነዘረች አየሁ፤ የፍችዋንም ደብዳቤ በእጅዋ ሰጥቼ ሰደድኋት፤ ጎስቋላ እኅቷ ይሁዳ ግን በዚያ አልፈራችም፤ እርስዋም ደግሞ ሄዳ አመነዘረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለከዳተኛዪቱ እስራኤል ስለ ምንዝርናዋ ሁሉ የፍች ወረቀቷን ሰጥቼ አባረርኋት። ከሓዲዋ እኅቷ ይሁዳም ይህን አይታ እንዳልፈራች አየሁ፤ ወጥታም አመነዘረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዳተኛይቱም እስራኤል ስላመነዘረች ስለዚህ ፈትቻታለሁ፤ የፍችዋንም ወረቀት ሰጥቻታለሁ፤ አታላይ እኅትዋ ይሁዳ ግን እንዳልፈራች እርሷም ደግሞ ሄዳ እንደ አመነዘረች አየሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤል እኔን ማምለክዋን ትታ የጣዖት አምልኮን ተከተለች፤ ይህንንም ስታደርግ የተውኳት መሆኔን ይሁዳ ተመልክታለች፤ እምነት የማይጣልባት የእስራኤል እኅት ይሁዳ ፍርሀት አላደረባትም፤ እርስዋም በበኩልዋ ጣዖት አምላኪ ሆናለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዳተኛይቱም እስራኤል ስላመነዘረች ስለዚህ ፈትቻታለሁ የፍችዋንም ወረቀት ሰጥቻታለሁ፥ አታላይ እኅትዋ ይሁዳ ግን እንዳልፈራች እርስዋም ደግሞ ሄዳ እንደ ጋለሞተች አየሁ። |
ደግሞም በይሁዳ ተራሮች ላይ መስገጃዎችን ሠራ፤ በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን እንዲያመነዝሩ አደረጋቸው፤ የይሁዳንም ሰዎች አሳታቸው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ደብዳቤ የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
ክፋትሽ ይገሥጽሻል፤ ክዳትሽም ይዘልፍሻል፤ እኔን መተውሽም ክፉና መራራ ነገር መሆኑን ታውቂያለሽ፤ ትረጂማለሽ” ይላል አምላክሽ እግዚአብሔር፤ “መፈራቴም በአንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላሰኘኝም” ይላል አምላክሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ ከእርሱም ዘንድ ሄዳ ሌላ ወንድ ብታገባ፥ በውኑ ደግሞ ወደ እርሱ ትመለሳለችን? ያች ሴት እጅግ የረከሰች አይደለችምን? አንቺም ከብዙ እረኞች ጋር አመንዝረሻል፤ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል እግዚአብሔር።
“ይህ ሕዝብ፦ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሁለቱን ወገን ጥሎአቸዋል፥ እንዲሁ በፊታቸው ከእንግዲህ ወዲህ ሕዝብ እንዳይሆን ሕዝቤን አቃልለዋል ያለውን ነገር አትመለከትምን?
“ከእነዚህ ነገሮች በየትኛው ይቅር እልሻለሁ? ልጆችሽ ትተውኛል፤ አማልክትም ባልሆኑ ምለዋል፤ አጠገብኋቸውም፤ እነርሱ ግን አመነዘሩ፤ በአመንዝራዎቹም ቤት ዐደሩ።
ታላቂቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በስተ ግራሽ የምትቀመጥ ሰማርያ ናት፤ ታናሽቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በሰተ ቀኝሽ የምትቀመጥ ሰዶም ናት።
አንቺ ግን በመንገዳቸው አልሄድሽም፤ እንደ ኀጢአታቸውም አላደረግሽም፤ ያው ለአንቺ ጥቂት ነበረና በመንገድሽ ሁሉ ከእነርሱ የሚከፋ ኀጢአት አደረግሽ።
ሰማርያም የኀጢአትሽን እኩሌታ አልሠራችም፤ አንቺ ግን ከእኅቶችሽ ይልቅ ኀጢአትን አበዛሽ፤ በሠራሽውም ኀጢአት ሁሉ አጸደቅሻቸው።
የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ምሥዋዕ፤ ያለ ካህንና ያለ ራእይ፤ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፤
“አንድ ሰው ሴትን ወስዶ ቢያገባ፥ የእፍረት ነገር ስላገኘባት በእርሱ ዘንድ ሞገስ ባታገኝ፥ የፍችዋን ጽሕፈት ጽፎ በእጅዋ ይስጣት፤ ከቤቱም ይስደዳት።
ሁለተኛውም ባል ቢጠላት፥ የፍችዋንም ጽሕፈት ጽፎ በእጅዋ ቢሰጣት ፥ ከቤቱም ቢሰድዳት፥ ወይም ሚስት አድርጎ ያገባት ሁለተኛው ባልዋ ቢሞት፥