La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 3:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቍጣው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራ​ልን? እስከ ፍጻ​ሜስ ድረስ ይጠ​ብ​ቀ​ዋ​ልን? እነሆ እን​ዲህ ብለሽ ተና​ገ​ርሽ፤ እንደ ተቻ​ለ​ሽም መጠን ክፉን ነገር አደ​ረ​ግሽ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሁልጊዜ ትቈጣለህን? ቍጣህስ ለዘላለም ነውን?’ አላልሽኝም? የምትናገሪው እንዲህ ነው፤ ይሁን እንጂ የቻልሽውን ክፋት ሁሉ ታደርጊያለሽ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

‘ለዘለዓለምስ ይቈጣልን? እስከ ፍጻሜስ ድረስ ይጠብቀዋልን?’ እነሆ፥ እንዲህ ብለሽ ተናገርሽ፥ እንደ ተቻለሽም መጠን ክፉን ነገሮች አደረግሽ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንቺ፦ ‘እርሱ ዘወትር ይቈጣልን? ኀይለኛ ቊጣውስ ዘላቂ ነውን?’ ብለሽ ተናግረሻል፤ ነገር ግን የምትችዪውን ክፉ ሥራ ትሠሪያለሽ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እስከ ፍጻሜስ ድረስ ይጠብቀዋልን? እነሆ፥ እንዲህ ብለሽ ተናገርሽ፥ እንደ ተቻለሽም መጠን ክፉን ነገር አደረግሽ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 3:5
14 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም የቍ​ጣ​ውን መቅ​ሠ​ፍት ከእኛ እን​ዲ​መ​ልስ ከእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ቃል ኪዳን አደ​ርግ ዘንድ በልቤ አስ​ቤ​አ​ለሁ።


አቤቱ፥ አንተ መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነህና፥ ይቅ​ር​ታ​ህም ለሚ​ጠ​ሩህ ሁሉ ብዙ ነውና።


አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን አድ​ምጥ፥ የል​መ​ና​ዬ​ንም ቃል ስማ።


“መን​ፈስ ከእኔ ይወ​ጣ​ልና፥ የሁ​ሉ​ንም ነፍስ ፈጥ​ሬ​አ​ለ​ሁና ለዘ​ለ​ዓ​ለም አል​ቀ​ስ​ፋ​ች​ሁም፤ ሁል​ጊ​ዜም አል​ቈ​ጣ​ች​ሁም።


አቤቱ፥ እጅግ አት​ቈጣ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን አታ​ስብ፤ አሁ​ንም እባ​ክህ፥ ወደ እኛ ተመ​ል​ከት፤ እኛ ሁላ​ችን ሕዝ​ብህ ነን።


ሂድና ይህን ቃል ወደ ሰሜን ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በል፦ ከዳ​ተ​ኛ​ዪቱ እስ​ራ​ኤል ሆይ! ወደ እኔ ተመ​ለሽ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ መሓሪ ነኝና፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አል​ቈ​ጣ​ምና በእ​ና​ንተ ላይ ፊቴን አላ​ጸ​ናም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሕዝቤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ ምን ወደ ኋላ​ቸው ተመ​ለሱ? ዐመ​ፅን ዐም​ፀ​ዋል፥ መመ​ለ​ስ​ንም እንቢ ብለ​ዋል።


አደ​መ​ጥሁ፤ ሰማ​ሁም፤ ቅንን ነገር አል​ተ​ና​ገ​ሩም፤ ማና​ቸ​ውም፦ ምን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ? ብሎ ከክ​ፋቱ ንስሓ የገባ የለም፤ የሚ​ሮ​ጠ​ውም ወደ ሰልፍ እን​ደ​ሚ​ሮጥ ፈረስ ሲሮጥ ደከመ።


“እነሆ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት አለ​ቆች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከዘ​መ​ዶ​ቻ​ቸው ጋር ደም ያፈ​ስሱ ዘንድ በአ​ንቺ ውስጥ ተባ​በሩ።


በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው! ኃይል በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል።


እጆቻቸውን ለክፋት ያነሣሉ፥ አለቃውና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፥ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጕናሉ።