አንቺስ፦ አልረከስሁም፤ በዓሊምንም አልተከተልሁም፤ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፤ ያደረግሽውንም ዕወቂ። ማታ ማታ በመንገዶች ትጮኻለች፤
ኤርምያስ 2:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከእኔ ጋር ለምን ትከራከራላችሁ? ሁላችሁ ክዳችሁኛል፤ ሁላችሁም ዐምፃችሁብኛል” ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለምን በእኔ ታማርራላችሁ? ያመፃችሁብኝ እናንተ ሁላችሁ ናችሁ፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከእኔ ጋር የምትከራከሩት ለምንድን ነው? ሁላችሁ ዐምፃችሁብኛል ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “ሁላችሁም ዐምፃችሁብኛል፤ ታዲያ ከእኔ ጋር የምትከራከሩት ስለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኔ ጋር የምትከራከሩ ለምንድር ነው? ሁላችሁ ዐምፃችሁብኛል ይላል እግዚአብሔር። |
አንቺስ፦ አልረከስሁም፤ በዓሊምንም አልተከተልሁም፤ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፤ ያደረግሽውንም ዕወቂ። ማታ ማታ በመንገዶች ትጮኻለች፤
ዐይኖችሽን አቅንተሽ አንሺ፤ ያልተጋደምሽበት ስፍራ እንዳለም ተመልከች። እንደ ምድረ በዳ ቍራዎች በመንገድ ላይ ተቀምጠሽ በዝሙትሽና በክፋትሽ ምድሪቱን አርክሰሻታልና።
“በኢየሩሳሌም መንገዶች ሩጡ፤ ተመልከቱም፤ ዕወቁም፤ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ ፍርድን የሚያደርገውን እውነትንም የሚሻውን ሰው ታገኙ እንደ ሆነ ይቅር እላቸዋለሁ ይላል እግዚአብሔር።
ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ኀጢአትን አድርገዋልና፥ ከሐሳዊ ነቢይ ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ሐሰትን አደረጉ።
አንደበት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚናገረው ሁሉ በኦሪት ላሉት እንደ ተነገረ እናውቃለን።